alt

ዓለም አቀፋዊ ይሁኑ

በመላው ዓለም ያሉ ምርጦች እና ብሩሆች ኢሞሪ ዩኒቨርሲቲን ይመርጣሉ። ኢሞሪ ዩኒቨርስቲ በደማቋ የአትላንታ ከተማ ውስጥ ወሳኝና ተመራጭ በሆነ ቦታ ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ ሰፊ የአጋርነት የመረጃ መረብ ዕድሎችን የሚሰጥ፣በትምህርት ጥራት፣ በአስደናቂ የምርምር ግኝት የአለምአቀፍ ማህበረስብን በማካተት የሚታወቅ ተቋም ነው።

ቀጣዩን ትውልድ ለዓለም አቀፋዊ አስተሳሰብ እና መሪነት ለማዘጋጀት በምናደርገው ጉዞ ይቀላቀሉን።

ስለኢሞሪ ዩኒቨርሲቲ የበለጠ ይረዱ

ስለኢሞሪ እውነታዎች እና አኃዛዊ መረጃዎች

ዘጠኝ ትምህርት ቤቶች፣ ከ15,000 በላይ ተማሪዎች፣ ወሰን የሌለው እምቅ አቅም

ሪፖርቱን ያንብቡ
Atlanta skyline over Emory

ከኢትዮጵያዊያን ባለሙያዎች ጋር አጋርነትን መፍጠር

ዶ/ር አበበ ገብረማሪያም በኢትዮጵያ ውስጥ የእናቶችና ጨቅላ ሕፃናት ጤና አጋርነት ፕሮጀክት ዳይሬክተርና ተባባሪ ተመራማሪ እንዲሁም የኢሞሪ -ኢትዮጵያ የሀገር ውስጥ አስተባባሪ/ተወካይ በመሆን ያገለግላሉ።

ዶ/ር አበበ ሥራቸውን የጀመሩት ኢትዮጵያ ውስጥ ሩቅ በሚባሉ የገጠር ከተሞች ጤና ጣቢያዎች ውስጥ ጠቅላላ ሐኪም በመሆን ሲሆን ዕድገት በማግኘት የወረዳ ጤና ኦፊሰር ቀጥሎም የክልል የጤና አጠባበቅ ፕሮግራም መምሪያ ኃላፊ በመሆን አገልግለዋል።

Abebe Gebremariam
ዶ/ር አበበ ገብረማሪያም